;

በሚኒሶታ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ በምክር እና በስነ -ልቦና አገልግሎት የማስተርስ ድግሪዬን አጠናቅቄአለሁ። እንደ አማካሪ እና ሰብዓዊ ፍጡር ፣ አንዳንድ የሕይወት ሁኔታዎችን ለብቻ መጋፋጥ እና ማሸነፍ እንዴት ፈታኝ ሊሆኑ እንደሚችል እረዳለሁ። በግላችን ከባድ ሁኔታዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ የስነ -ልቦና አማካሪ ድጋፍ መፈለግ ጥሩ አማራጭ እና መልካም ውሳኔ ነዉ።
እንደ አንድ ክርስቲያን የስነ-ልቦና አማካሪ ለክርስትና እምነት ተከታይ ለሆኑ ተገልጋዮቼ በምርጫቸዉ መፅሀፍ ቅዱሳዊ እንዲሁም መንፈሳዊ መሰረት ያላቸው የስነ-ልቦና ማማከር አገልግሎት እሰጣለሁ።
በአማርኛ ቋንቋ በሚገባ ሁኔታ መግባባት ስለምችል ቋንቋውን ለሚናገሩ ሰዎች እና የስነ-ልቦና ማማከር አገልግሎቱን በአማርኛ እንዲሆን ለሚፈልጉ ሰዎች አገልግሎቱን በአማርኛ ቋንቋ ለመስጠት ፈቃደኛ ነኝ።
የማማከር አገልግሎቱ ከሚያካትታቸው የስነ-ልቦና ችግሩሮች መካከል ከልክ ያለፈ ጭንቀት፣ የድብርት ስሜት፣ አሰቃቂ ተሞክሮ ፣ የማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ ያሉ ችግሮች ፣ ከልጆች አስተዳደግ ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች እንዲሁም በተለያዮ ምክንያቶች የሚፈጠሩ የህይወት መቃወሶችን ይጨምራል።
የእያንዳንዱ ሰው የኑሮ ተሞክሮ እና ተግዳሮቶች የተለያዮ በመሆናቸው ተገልጋዬች የሚሰማቸውን ስሜት በግልፅና በነፃነት ማጋራት የሚችሉበትን የተመቻቸ ሁኔታ በማዘጋጀት ለችግሮቻቸው መፍትሄ በጋራ እንሰራለን። እንዲሁም በተለያዩ የዕድሜ ክልል ከሚገኙ የስነ -ልቦና የማማከር አገልግሎት ከሚፈልጉ ተገልጋዬች ጋር አብሮየመስራት ልምድ አለኝ።